ሀገሬ ቲቪ

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ 1 ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበር የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ 1 ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበር የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ደግሞ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በአስገዳጅነት እንዲከወን ይደረጋል ተብሏል፡፡

የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ።

ከዚህ ቀደም የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱ ተጠቁሟል።

በባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀሙም ተነስቷል።

የነዳጅ ግብይቱ በኤሌክትሮኒክስ መላ መሆኑ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ ያደርግል ተብሏል፡፡

ሕብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈፀም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ተነግሯል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-07