ሀገሬ ቲቪ

ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023 ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከ600 በላይ የውጭ ባለሀብቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነገረ፡፡

ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023 ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከ600 በላይ የውጭ ባለሀብቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነገረ፡፡

ፈረሙ ከሚያዚያ 18 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።

የፎረሙ አላማ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ማስተዋወቅ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን ገልፀዋል።

ፎረሙ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-10