ሀገሬ ቲቪ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከታች ባሉ የትምህርት ሴክተሮች ላይ ከፍተኛ የዕውቀት ሽግግር ክፍተት መኖሩ ተጠቆመ።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከታች ባሉ የትምህርት ሴክተሮች ላይ ከፍተኛ የዕውቀት ሽግግር ክፍተት መኖሩ ተጠቆመ።

በርካታ ጥናት እና ምርምሮች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየግዜው ቢደረጉም፤ በመዋዕለ ሕፃናት እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መምህራን እንዲያውቋቸው የማደረጉ ተግባር እንደሌለ የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግራቸው ጋሻው ለሀገሬ ነግረውናል።

የትምህርት ሚንስቴር በበኩሉ ክፍተቱ መኖሩ በደንብ ይታወቃል ያለ ሲሆን፤ ክፍተቱን ይሞላል የተባለ የዲጂታል ኢዱኬሽን እስትራቴጂ ተቀርፆ በውይይት ላይ እንደሚገኝ በተለይ ለሀገሬ ነግረውናል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-04-11