ሀገሬ ቲቪ

20 ቢሊየን ብር ከታክስ ስወራ ማዳኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

20 ቢሊየን ብር ከታክስ ስወራ ማዳኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት በውስን ተቋማት ላይ ባደረገው ኦዲት ከ20 ቢሊየን ብር በላይ መጭበርበሩን አስታውቋል።

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ ለሀገሬ ቲቪ እንዳሉት ሶስት ድርጅቶች ሀሰተኛ ደረሰኝን ሲጠቀሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል።

የሀሰትኛ ደረሰኝ መበራከት ሀገር የምታገኘውን የታክስ ገንዘብ በአግባቡ እንዳታገኝ እያደርገ መሆኑንም አንስተዋል።

የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከፍተኛ የሆነ የታክስ ማጭበርበር እንደሚስተዋልባቸው የስራ ዘርፎች መሆናቸውንም አቶ ሲሳይ ጠቁመዋል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-04-11