
ካሜሮን ወደ አጎአ ለመመለስ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች፡፡
ካሜሮን የውጭ ምንዛሬ ገቢዋ በማሽቆልቆሉ ምክንያት የውጭ ንግዷን ለማስፋፋት ወደ አጎአ መመለስ እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ወደ አጎአ ለመግባት ከዋሽንግተን ጋር መነጋገር መጀመሯን የኢኮኖሚ ሚኒስቴሯ ገልጿል።
እያሽቆለቆለ የሚገኘውን መጣኔ ሀብቷን ለመታደግ ከቀረጥ ነፃ ገበያውን ለመጠቀም ማማተሯን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ካሜሮን በፈረንጆቹ 2019 በሀገሪቱ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከአሜሪካ ለአፍሪካ ከሰጠችው የአጎአ እድል ሰርዛት እንደነበር ይታወሳል።
በማህሌት አማረ
2023-04-11