ሀገሬ ቲቪ

እንግሊዝ መልሻለው ያለችው የናይጄሪያ ገንዘብ

እንግሊዝ ከናይጄሪያ የተዘረፈ ወደ 23 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መልሻለው ብላለች። ገንዘቡ እንደ ምዕራባውያኑ በ1990ዎቹ ናይጄሪያን ይመሩ በነበሩት ሳኒ አባቻ እና ቤተሰቦቻቸው ከሀገሪቱ የተዘረፈ ነው። በጉዳዩ ላይ የናይጄሪያ መንግስት እስካሁን ያለው ነገር የለም። አምባገነን ናቸው የሚባልላቸው አባቻ ናይጄሪያን ባስተዳደሩበት ወቅት የሀገሪቱን ረብጣ ሚሊዮኖችን በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚገኙ ባንኮች በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ስም አስቀምጠዋል። ናይጄሪያ እንደ ምዕራባውያኑ በ 2006 በእኚሁ ሰው የተዘረፈ ወደ 723 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከስዊዘርላንድ እንዲመለስ አድርጋለች።

በሳምሶን ገድሉ
2022-05-10