ሀገሬ ቲቪ

የዘንድሮ አጠቃላይ የሐጅ መስተንግዶ ዋጋ 315 ሺህ ብር መሆኑን ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

የዘንድሮ አጠቃላይ የሐጅ መስተንግዶ ዋጋ 315 ሺህ ብር መሆኑን ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

የዘንድሮው ጉዞ ለ1 ሺህ 444ኛ ጊዜ ሲሆን ከበፊቱ አንፃር የመስተንግዶው ዋጋ መወደዱ ተነግሯል፡፡

የመስተንግዶ ዋጋው የጨመረው የውጭ ምንዛሪ፣ የመዳረሻ ቦታዎች ክፍያ በመጨመራቸው እና ለዘመናዊው የሐጅ ምዝገባ ሥርዓት አስተዳደራዊ ወጪ መጠየቁ እንዲሁም የተጓዥን ምቾት ለመጠበቅ ሲባል ዘመናዊ ማረፊያ ሆቴሎች ኪራይ በመያዛቸው ነው ተብሏል፡፡

የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ መስተንግዶና ምዝገባ አገልግሎት ተዓማኒና ከእንግልት ነፃ በሆነ መልኩ እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-12-04