ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተጋነነ የመሬት ካሳ ክፍያ በመጠየቄ የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታን መጀመር አልቻልኩም ሲል ተናገረ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተጋነነ የመሬት ካሳ ክፍያ በመጠየቄ የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታን መጀመር አልቻልኩም ሲል ተናገረ፡፡

ለግንባታው የተመረጠው ቦታ አርሶ አደሮች በመስኖ የሚያለሙበት በመሆኑ ለ25 ሄክታር መሬት 525 ሚሊዮን ብር በካሳ መመሪያው መሰረት እንዲከፍል መጠየቁን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በዚህም ምክንያት ከታቀደ ከአምስት ዓመታት በላይ የሆነው የማስፋፊያ ግንባታው እስካሁን አለመጀመሩ ተነግሯል፡፡

አጠቃላይ ግንባታውን ለማከናወን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚፈጅ እና ይህ ባለበት ሁኔታ የተጠየቁት ካሳ ተገቢ አለመሆኑን በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የወደብና ተርሚናል አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረተአብ ተክሉ ተናግረዋል፡፡

የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታ እንዲገነባ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ፍላጎት አለው ያሉት ከንቲባው፤ ነገር ግን የአርሶ አደሩን እና የአገልግሎቱን ፍላጎት ማጣጣም አልተቻለም፤ በዚህም የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታ ሳይጀመር ቀርቷል ብለዋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-17