ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 100 ንፁሃን ዜጎች መሞታቸውን የዶክተሮች የሰራተኛ ማህበር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በሱዳን በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 100 ንፁሃን ዜጎች መሞታቸውን የዶክተሮች የሰራተኛ ማህበር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው የሀገሪቱን መደበኛ ኃይልና ፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይልን በሚመሩት በሁለት የጦር ጀነራሎች መካከል የነበረው አለመግባባት በመካረሩ ነው።

በሱዳን የሽግግር አስተዳደር ምክር ቤት መሪ ጀነራል አብዱል ፋታህ እና የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል አዛዡ ጀነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ መካከል የቆየው አለምግባባት ወደ ለየለት ግጭት አምርቶ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ሀገሪቱ በጥይት ድምፆች እየተናጠች ነው፡፡

በጀነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኃይል የሱዳን የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤትን፣ የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ እና ሌሎች የሀገሪቱን ቁልፍ ቦታዎች መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሱዳን የተፈፀመውን ግጭት አውግዘዋል፡፡

የዓለም አቀፉን የምግብ ድርጅት ሶስት ሰራተኞችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ህይወት ያለፈበትን ግድያ አፋጣኝ ፍትህ ጠይቀዋል።

በናርዶስ ታምራት
2023-04-17