ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ የጦር መርከቦቿን በታይዋን የባህር ወሽመጥ ማስጠጋቷ ተገለፀ፡፡

አሜሪካ የጦር መርከቦቿን በታይዋን የባህር ወሽመጥ ማስጠጋቷ ተገለፀ፡፡

አሜሪካ የቻይናን ወታደራዊ ልምምድ ተከትሎ በታይዋን የባህር ወሽመጥ በኩል የባህር ኃይሏን ማሰማራቷ ተነግሯል።

በርኬ-ክላስ የሚመራ አንቲ ሚሳዬል የጫኑ 7 የጦር መርከቦቿን ማስጠጋቷ ነው የተነገረው።

ቻይናም የአሜሪካንን የጦር መርከብ በባህር ወሽመጦቹ በኩል ሲያልፉ አስተውያለሁ ብላለች፡፡

የቻይና መከላከያ ቃል አቀባይ ኮሌኔል ሺ ዩ በባህር ወሽመጡ አካባቢ ያሉ የቻይና ወታደሮች ሁሌም በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ወታደሮቹ ለሀገራቸው ሉዓላዊነት እና ደህንነት እንዲሁም የህዝባቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚታገሉ ተናግረዋል ሲል የዘገብው አልጀዚራ ነው።

በማህሌት አማረ
2023-04-17