ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሶቹን አውቶቡሶች ጨምሮ በቀን 900 የሚሆኑ ይሰማራሉ ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሶቹን አውቶቡሶች ጨምሮ በቀን 900 የሚሆኑ ይሰማራሉ ተባለ።

አሁን ላይ አንበሳ እና ሸገር አውቶብሶች 187 በሚበልጡ መስመሮች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን እና በቀን 900 የሚደርሱ አውቶብሶችን በማሰማራት ከ850 ሺህ በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የአገልግሎቱ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሙኤል ፍስሃ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ተገዝተው የገቡት አውቶብሶችም የትራንስፖርት ችግር በሚስተዋልባቸው መስመሮች ላይ ተመድበው የማህበረሰቡን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ ረገድ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አንስተዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የሥነ ምግባር ችግሮችን ለማስገወድም በሰራተኞች ላይ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ነው የሚናገሩት።

የአውቶብስ ተጠቃሚዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግሮች ሲመለከቱም በነፃ የስልክ መስመር 8981 ላይ በመደውል ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-17