የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ ከሱዳን አምባሳደር ጀማል ኤል ሼክ ጋር መወያየታቸው ተገለፀ፡፡ .
በውይይታቸው በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተጠቅሷል።.
አምባሳደር ምስጋኑ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ኢትዮጵያን በእጅጉ እንዳሳሰባት ተናግረዋል፡፡.
በሁለቱ ወንድማማች አካላት መካከል የተፈጠረው ግጭት በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡.
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እና ዲፕሎማቶች አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያገኙ እምነታቸው መሆኑንም በመግለፅ የተከሰተውን ችግር በሱዳናውያን አቅም በሰላማዊ ውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡.
በብሩክታዊት አስራት
2023-04-18
