የሱዳን ህዝብ አሁን ካጋጠመው ሁኔታ ለመውጣት የሚያስችለው ጥበብና ችሎታ ያለው ህዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ።
የሱዳን ህዝብ በባህሪው ኩሩ በመሆኑ በምንም ሁኔታ ክብሩን እና ነፃነቱን አሳልፎ የሚሰጥ አያደርገውም ስለሆነም የሱዳን ህዝብ የራሱን ችግር በራሱ የመፍታት ታላቅ ዓቅም እና ጥበብ ያለው ታላቅ ህዝብ በመሆኑ ማንኛውም የሁከት ዓላማን ያነገበ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያስተናግድ አይሆንም ብለዋል።
የሱዳን ህዝብ የራሱን ችግር በራሱ እንዲፈታ መተው ያለበት ሲሆን የማንኛውም የውጭ ጣልቃ ገብነት ዓላማም ሰላምን እና ድርድርን በተመለከተ ብቻ ሊሆን ይገባል እንላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከዛ ውጭ በሆነ በማንኛውም ድብቅ አጀንዳ የተነሳሳ የጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴ በታሪክ ሸንጎ ላይ ተጠያቂ የሚያደርግ ይሆናልም ሲሉ ተናግረዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2023-04-18
