ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ያሰለጠነቻቸውን ተማሪዎች ልታስመርቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ያሰለጠነቻቸውን ተማሪዎች ልታስመርቅ ነው፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ካበረከቱ ሀገራት መካከል አንዷ ብትሆንም እስካሁን ድረስ ግን የቡና ሳይንስ ምሁራን እንዳላፈራች ተገልጿል።

የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 እንዲከፈት ማድረጉን ተናግረዋል።

በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ቡናን በትምህርትና ምርምር አስደግፎ ለመምራት ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የቡና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ማቋቋሙንም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

በሚቀጥለው ዓመት በሁለተኛ ዲግሪ በቡና ሳይንስ ተማሪዎች ይመረቃሉ ያሉት ዶክተር ጴጥሮስ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዜትም የቡና ሳይንስ ትምህርት መስክን በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ማስተማር እንደሚጀምር መናገራቸውን አል አይን አማርኛ ዘግቧል።

በናርዶስ ታምራት
2023-04-18