ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላማዊ ሰልፎችን ማክበር እንዳለበት አምነስቲ አሳሰበ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላማዊ ሰልፎችን ማክበር እንዳለበት አምነስቲ አሳሰበ።

በአለም ዙሪያ ስለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚሰራው አለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላማዊ ሰልፎችን ማክበር እንዳለበት እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰባት የሚዲያ ባለሙያዎችም በፍጥነት እንዶለቀቁ ጠይቋል።

የክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ስራው በተጀመረበት ወቅት በአማራ ክልል የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በክልሉ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ ነው ያለው፡፡

አምነስቲ መንግሥት ሰልፈኞችን ከማሰር ይልቅ የሐሳብ ነፃነታቸውን አክብሮ ጥያቄቸውን መመለስ አለበት ብሏል።

የሚዲያ ባለሙያዎችም ስራቸውን በነፃነት እንዲሰሩ መፍቀድ አለበት ሲል አምነስቲ አሳስቧል።

በማህሌት አማረ
2023-04-18