ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የበጀት ጉደለቷን መሙያ 2 ቢሊየን ዶላር ብድር እንደምትሻ ተገለፀች።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የበጀት ጉደለቷን መሙያ 2 ቢሊየን ዶላር ብድር እንደምትሻ ተገለፀች።

ሀገሪቱ ከፋይናንስ ተቋሙ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ ለገጠማት የዶላር እጥረት መፍትሄ ልታገኝ ትችላለች ተብሏል።

በገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ ቡድን በዋሽንግተን ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም ኃላፊዎች ጋር እየተደራደረ ነው።

በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት ያስቀጠለው ይህ ድርድር ከተሳካ ኢትዮጵያ የበጀት ጉድለቷንም ሆነ የዶላር እጥርቷን የሚቀርፍላት እስከ 4 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ብድር ልታገኝ ትችላለች ተብሏል።

የብድር ጫናዋ ከፍ ማለቱ እና የገንዘብ ተቋማቱ የሚያቀርቡት ቅድመ ሁኔታ መብዛት ለብድሩ መሳካት እንቅፋት እንዳይሆን ተሰግቷል።

ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የበጀት ጉድለቷ 6 ቢሊየን ዶላር እንድሚደርስ ትበያዎች ያሳያሉ፡፡

በብሩክ ያሬ
2023-04-18