
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ሥራ ለመጀመር ዝግጁ መሆኑ ተነገረ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይጄሪያ መንግሥት ጋር ባደረገው የንግድ ስምምነት መሠረት፤ በናይጄሪያ ሥራ ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለአቪያ ዴቭ ኢንሳይት አፍሪካ ድረገፅ ተናግረዋል።
ነገር ግን አንድ የፍርድ ቤት ጉዳይ መኖሩ ብቸኛ እንቅፋት ነው የተባለ ሲሆን፤ የናይጄሪያን አየር መንገድ በአዲስ መልኩ ለማደራጀት አሁን ላይ የስምምነት ሂደቱ በጣም ጥሩ መሻሻል የታየበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በናይጄሪያ አየር መንገድ የባለቤትነት መዋቅር የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ አብላጫውን ድርሻ የያዘ ሲሆን፤ ሦስት የናይጄሪያ የአገር ውስጥ ድርጅቶች 46 በመቶ እንዲሁም የናይጄሪያ መንግሥት 5 በመቶ ድርሻ አለው፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-04-19