ሀገሬ ቲቪ

መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከመንግሥት ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከመንግሥት ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግሥት በመጪው ማክሰኞ ከሸኔ ጋር በታንዛኒያ ድርድር ማድረግ እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን በስነ ስርዓቱ ላይ መንግሥት ከሸኔ ጋር ከመጭው ማክሰኞ ጀምሮ በታንዛኒያ ድርድር እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው የሽብር ቡድን በበኩሉ የቀረበውን የድርድር ሀሳብ እንደሚደግፍ ገልፆ በድርድሩ ተሳታፊ እንደሚሆን ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

ቡድኑ በገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የሚደረግ ድርድር ለሰላም ሂደቱ በጎ ሚና ይኖረዋል ብሎ እንደሚያስብ ገልጿል፡፡

በይስሐቅ አበ
2023-04-24