የአክሲዮን ገበያ ትምህርት ለመስጠት እየተሰራ ነው።
የአክሲዮን ገበያን መሰረት ያደረገ ትምህርት ለመስጠት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ ከወራት በኃላ አክሲዮን ገበያን እንደሚጀመር የገለፀ ሲሆን እስካሁን 600 ባለሞያዎችን አሰልጥኖ ዓለም አቀፍ ሰርተፍኬት እንዲይዙ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ከሀገሬ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለስልጣኑ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ዳንኤል አንበርብር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ስራ ኮሌጅ ከዓለም አቀፍ ትምህርት ተቋማት ጋር ባደረገው ስምምነት በአክሲዮን ገበያ ላይ የትምህርት ክፍል ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ አንስተዋል፡፡
በይስሐቅ አበ
2023-04-25
