ሀገሬ ቲቪ

ቱርክ በሱዳን ያሉ ዜጎቿን ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን ማስወጣት መጀመሯ ተጠቆመ፡፡

ቱርክ በሱዳን ያሉ ዜጎቿን ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን ማስወጣት መጀመሯ ተጠቆመ፡፡

በሱዳን ፈጠኖ ደራሽ ኃይል እና በሱዳን ጦር መካከል ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት ቱርክ ዜጎቿን በሶስት ቡድን በመክፈል በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት መጀመሯ ተነግሯል።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በስልክ መወያየታቸውን የቱርክ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በሱዳን በተቀሰቀሰ ግጭት እስካሁን ድረስ 413 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 3,500 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በማህሌት አማረ
2023-04-25