ቻይና ጥያቄ ያስነሳባትን የአምባሳደሯን ንግግር አስተባበለች።
በፈረንሳይ የቻይና አምባሳደር ሉ ሻዬ ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ እ.ኤ.አ. በ2014 ሩስያ ከዩክሬይን የነጠቀቻትን ክሪሚያን በተመለከተ የዩክሬይን ግዛት ስለመሆኗ የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፋዊ ህግ የለም ማለታቸው ቻይና ላይ ጥያቄ አስነስቷል።
ቻይና የሀገራትን ሉዓላዊነት ይጋፋል ስለተባለው የአምባሳደሯ ንግግር በተደጋጋሚ ለቀረበላት የማብራሪያ ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሀገራቸው ከሶቭየት ሪፐብሊክ መፍረስ በኋላ የተፈጠሩ ሀገራትን ሉዓላዊነት እንደምታከብር ገልፀዋል።
በአብርሃም በለጠ
2023-04-25
