ኢትዮ ቴሌኮም በዓለማችን የመጨረሻው የሆነውን የኢንተርኔት አይነት በሀገሪቱ በትናንትናው ዕለት ማስጅመሩን ይፋ አድርጓል። ይህ የኢንተርኔት አይነት 5ጂ አልያም አምስተኛው ትውልድ ይሰኛል ። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛው ትውልድ አሊያም (5G) የሞባይል ኔትዎርክ በዕለት ተለት ሕይወታችን ውስጥ በሚያስፈልጉን የሥራ መስኮች ፈጣን እና እጅግ ቀልጣፋ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ይረዳል። የዓለማችን 7 በመቶ ሕዝብ ብቻ 5G የሞባይል ኔትዎርክ ይጠቀማል። በአህጉራችን ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ፣ ሌሶቶ፣ እና ዩጋንዳ ይኽን የሞባይል ኔትዎርክ መጠቀም ጀምረዋል። በዓለማችን 70 ሀገራት በአኅጉራችን 6 ሀገራት ብቻ የሚጠቀሙት 5G ኔትወርክ ሀገሪቱ ዓላማ ላደረገችው ምርታማነትን ማስፋት ትልቅ ደጀን እንደሆነ ነው የተነሳው ነገር ግን አሁን ላይ ያለው 4ኛ ትውልድ ኔትወርክ መቼ ተዳራሰና ነው ወደ አምስተኛው የገባነው የሚል ጥያቄ ከተነሳ በቂ ምክንያት አለን ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ። በሀገሪቱ ካሉ 64 ሚሊዮን ደንበኞች አንድ መቶ አስር ሺሕ የሚሆኑት ብቻ ናቸው 5ጂ ኔትወርክን ለመጠቀም የሚያስችል የስልክ ቀፎ ያላቸው ። በቀጣይ 12 ወራት ውስጥ 150 የሚሆኑ የ 5ጂ ሳይቶች በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጪ ይኖረናል ብሏል ኢትዮ ቴሌኮም።
በሙሉጌታ በላይ
2022-05-10
