ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ ሚያዚያ 21 ቀን በእንጦጦ ፓርክ ይካሄዳል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ ሚያዚያ 21 ቀን በእንጦጦ ፓርክ ይካሄዳል ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2023 በማስመልከት ለመጀመርያ ጊዜ ለሚካሄደው ኢትዮጵያ ታምርት የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ቅዳሜ ሚያዝያ 21 ቀን በእንጦጦ ፓረክ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። ይህ ልዩ ዝግጅት የ5 ኪሜ ሩጫ ሲሆን ለሁሉም ችሎታዎች ተሳታፊዎች ክፍት መሆኑ ተነግሯል፡፡ በሩጫው እስከ 3000 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡ በሩጫዉ ላይ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ አትሌቶች ከ100 ሺህ ብር ጀምሮ ሽልማት መዘጋጀቱ ታዉቃል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-25