ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ኢትዮጵያ ምርቶቿን በብዛት ለመሸጥ እና ተደራሽነትታቸውን ለማስፋት ያግዛታል ተባለ።

የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ኢትዮጵያ ምርቶቿን በብዛት ለመሸጥ እና ተደራሽነትታቸውን ለማስፋት ያግዛታል ተባለ።

ሀገሪቱ ከወጪ ንግዷ 70 በመቶ የሚሆነው የምትልከው ከአፍሪካ ውጪ ወዳሉ አህጉራት እንደሆነ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዴዔታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል።

በተጨማሪ የአፍሪካ የእርስ በእርስ የንግድ ትስስሩ ከ15 በመቶ እንደማይበልጥ ነው ዴዔታው የገለፁት፡፡

አህጉራዊ የንግድ ቀጠናው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሲሆን የንግድ ትስስሩን ግንከዚህ የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልፀዋል።

ኢትዮጽያ የንግድ ስምምነቱን ቀድመው ከፈረሙ ሀገራት መካል እንዷ መሆኗንም ተናግረዋል።

አህጉራዊ የንግድ ቀጠናው 30 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ከድኅነት ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ትሬድ ማርክ አፍሪካ በጋራ በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ጀምሯል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-04-26