በመንግሥት እና በሸኔ መካከል የሚደረገው ድርድር በትናንትናው እለት በታንዛኒያ መጀመሩ ተገለፀ።
ድርድሩ በታንዛኒያ ከፊል ራስ ገዟ ዛንዚባር መጀመሩን የኢጋድ ቃል አቀባይ መናገራቸውን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።
በታንዛኒያ እየተካሄደ ያለው ንግግር ወደ ስምምነት ያደርሳል ብለው እንደሚጠብቁ የኢጋድ ቃል አቀባይ ኑር ሞሃመድ ሼክ ጠቁመዋል።
የሸኔ ቃል አቀባይ ኦዳ ቶርቤ ለአሶሼትድ ፕረስ በሰጠው መረጃ የመጀመሪያ ውይይት ትኩረቱን መተማመን በሚፈጠርባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጉን አስታውቋል።
ከፌዴራል መንግሥት ስለ ውይይቱ ሂደት እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
በይስሐቅ አበ
2023-04-26
