ሀገሬ ቲቪ

ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ባለስልጣናት መቀሌ ገብተዋል፡፡

ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ባለስልጣናት መቀሌ ገብተዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ልዑካን ቡድን መቀሌ ገብቷል፡፡
ልዑኩ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን ያካተተ ነው።
ልዑካን ቡድኑ መቀሌ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
የጉዞው ዓላማ በትግራይ ክልል የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ክልሎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እና የሰላም ጅማሮውን በተግባር ለማስቀጠል ነው ተብሏል።

በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-04-27