
በሱዳን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊደረግ የሚችለው ድጋፍ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በካርቱም የኢትዮጵያ ኢምባሲ የሚገኝበት አካባቢ የውጊያ ቀጠና በመሆኑ በአካባቢው የመብራት አገልግሎት መቋረጡ እና የምግብ አቅርቦት ለማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑ ተገልጿል።
በስፍራው ያለው ሁኔታ ዜጎችን ለመርዳት አስቸጋሪ ስላደረገው የዲፕሎማቶችም ህልውና አደጋ ላይ ስለሚወድቅ በኤምባሲው የተወሰኑ ሰራተኞች እንዲቀሩ ተደርጎ አምባሳደሩ እና ሌሎች ሰራተኞች በገዳሪፍ ስራቸውን እያከናወኑ እንደሚገኙም ተመልካቷል።
በአብርሃም በለጠ
2023-04-27