ሀገሬ ቲቪ

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ እጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል የሚሞክሩ ማደያዎች መኖራቸውን ደርሸበታለሁ አለ።

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ እጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል የሚሞክሩ ማደያዎች መኖራቸውን ደርሸበታለሁ አለ።

በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ ያለው ባለስልጣኑ የነዳጅ እጥረት ይከሰታል የሚሉ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

በቀጣይም እጥረት ያለ ለማስመሰል የሚጥሩ ማደያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል።

የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት መጀመሩን ተከትሎ የአሽከርካሪዎች ግብይቱን ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት አለመኖር ለሚታዩት ሰልፎች ምክንያት እንጂ የነዳጅ እጥረት አይደለም ብሏል።

በአብርሃም በለጠ
2023-04-27