ሀገሬ ቲቪ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን እና ከጀኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ዋና አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ይገባዋል ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በሳምሶን ገድሉ
2023-04-28