ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ተጨማሪ የውጪ ቋንቋዎችን በዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎቱ ላይ ማካተቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ተጨማሪ የውጪ ቋንቋዎችን በዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎቱ ላይ ማካተቱን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎቱ ላይ አረብኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን ነው ያካተተው።

ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ የቋንቋ ተደራሽነት ላይ መስራቱ በዓለም አቀፉ የአቭየሽን ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚጠቅመው ተናግረዋል።

የደንበኞች አገልግሎቱ ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነም ነው የተነገረው።

በሳምሶን ገድሉ
2023-04-28