
በሱዳን ብሄራዊ ጦር እና ፈጠኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ወደ ጦር ሜዳነት የተቀየረችው ሱዳን በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿ ወደ ግብፅ መሰደዳቸው ተሰምቷል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም 14ሺህ የሚሆኑ ሱዳናዊያን ወደ ግብፅ መግባታቸውን አረጋግጧል።
2000 የሚሆኑ የሌሎች ሀገራት ዜጎች እና የአለም አቀፋዊ ተቋማት ሰራተኞችም ግብፅ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
እስካሁን በሱዳን ተባብሶ በቀጠለው ጦርነት ከ512 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 4200 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በማህሌት አማረ
2023-04-28