ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የፍጥነት ወሰን በጣሱ ከ17 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የፍጥነት ወሰን በጣሱ ከ17 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም 211 ሰዎች በመንገድ ትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ሲያጡ 911 ሰዎች ከባድ ና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡

የትራፊክ አደጋ ለተወሰነ አካል የሚሰጥ ኃላፊነት ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተነግሯል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2023-05-01