በደም ጥራት ወይም በአጥንት ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን አግላይ ፖለቲካ ለሰራተኞች መብቶች መጣስ ዋናው መንሳኤ ነው ሲል ኢዜማ ገለፀ፡፡
ፓርቲው የላብ አደሮችን ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው አሁን ባለው የሀገራችን ነባራዊ የፖለቲካ ስርዓት ምክንያት ቀደም ተብለው በሰራተኛው ከሚነሱ ጥያቄዎች በዘለለ የከፋ ችግር ይታያል።
ሰራተኞች የተመቻቸ የሥራ ሁኔታን ከመጠየቅ ይልቅ የሚገኙ የሥራ ዕድሎችን ለመጠቀም በሀገሪቱ ግዛቶች ተንቀሳቅሰው መስራት እና ሃብት ማፍራት ስጋት ሆኖባቸው ይስተዋላል።
መብቶቻቸውን ለማስከበር እና በመንግሥት የሚቀረፁ ፖሊሲዎች ላይ ጫና ለማሳረፍ እንዳይችሉ በሰራተኛው ስም የተደራጁት ማህበራት በመንግሥት ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ምክንያት ሲዘወሩ እና ለአብዛኛው ሰራተኛ ጥቅም ጥረት ከማድረግ ይልቅ በማህበራቱ ውስጥ ያሉ ሽኩቻዎች ጎልተው ይታያሉ ብሏል ፓርቲው።
ሀገራችን በውስጥ ፖለቲካ ያጋጠማት በደም ጥራት/አጥንት ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን አግላይ ፖለቲካ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ የሰራትኞችን መብት እና ጥቅም ለመረጋገጥ ቁልፉ መፍትሄ ስለመሆኑም ፓርቲው አመላክቷል።
በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-05-01
