ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ ሱዳን መልዕክተኛ መላኩን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ ሱዳን መልዕክተኛ መላኩን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ድርጅቱን የወከሉ መልዕክተኞችን ወደ ሱዳን መላካቸው ተነገረ።

ወደ ሀገሪቱ የሚያቀኑ መልዕክተኞችን የሚያስተባብሩት የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፍትስ በሰጡት መግለጫ የሱዳን “የሰብዓዊነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል።

"በአንድ ሌሊት ህይወታቸው ለተመሰቃቀለ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች አፋጣኝ እፎይታ ማምጣት የምንችልበትን መንገድ ለመቃኘት ወደ ሱዳን እናቀናለን" ብለዋል።

ይሁን እንጂ በሰብአዊ አገልግሎት መስጫ መሥሪያ ቤቶች እና መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ ዘረፋ ሲፈፀም አብዛኞቹ አቅርቦቶች በመዘረፋቸው የጉዳቱ ሰለባዎች የሚታገዙበትን ሁኔታ በአስቸኳይ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል።

በናርዶስ ታምራት
2023-05-01