ሀገሬ ቲቪ

ቱርኩ የአይ ኤስ ኤስ ቡድን መሪ መገደሉን አስታወቀች፡፡

ቱርኩ የአይ ኤስ ኤስ ቡድን መሪ መገደሉን አስታወቀች፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኢርዶጋን የአይ ኤስ ኤስ ቡድን መሪ አቡ አል ሁሴን አል-ሁሰኒ መገደሉን አስታውቀዋል።

ኤርዶጋን እንዳስታወቁት ከሆነ የቱርክ የምርመራ ቡድን የኤስ ቡድን መሪ የነበረው አቡ አል ሁሴንን ላይ ለረጅም ጊዜ ክትትል ሲያደረግ እንደነበር ተናግረዋል።

የአይ ኤሱ መሪ የተገደለው በሰሜናዊ ሶሪያ ግዛት አሌፖ ከተማ አቅራቢያ ውስጥ እንደሆነ የቱርክ የደህነነት መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ኤርዶጋን ከቱርክ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምንም ዓይነት አድልዎ ሳናደርግ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር የምናደርገውን ትግል እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-05-01