የዓለም የምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ የሚልከውን እርዳታ እንዳቋረጠ ተገለፀ፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለእርዳታ በሚቀርበው የምግብ እህል ላይ የሚፈፀመውን ስርቆት ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።
በዚሁ ምክንያት ወደ ትግራይ ክልል የሚልከውን የምግብ እህል እርዳታ በጊዜያዊነት ማቆሙን የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ተናግረዋል።
ሁለት ዓመት ያህል በዘለቀው በሰሜኑ ጦርነት በትግራይ ክልል የተባበሩት መንግሥታት እና ከሌሎች አጋር ለጋሾች የሚመጡትን እርዳታዎች በኃላፊነት ሲያከፋፍል ቆይቷል።
በዚህም የእርዳታ እህሎች ስርቆት እንደገጠመው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ማስታወቁ አይዘነጋም።
በማህሌት አማረ
2023-05-02
