በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ለዓመታት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም መጀመሩ ተሰምቷል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ ነበር።
በትግራይ 85 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከባድ እና ከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ባለው ነገር ትምህርት ቢጀምሩም አሁንም የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተፈናቃይ ዜጎችን አስጠልለው እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በማህሌት አማረ
2023-05-02
