ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት የ42 ሀገራት ዜጎች በምዕራብ ጎንደር መተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ገልጿል።

በሱዳን በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት የ42 ሀገራት ዜጎች በምዕራብ ጎንደር መተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ቢሆነኝ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ የ42 ሀገራት ዜጎች መግባታቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ ውስጥ 941 ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል።

ተፈናቃዮቹ የጤና ችግር እንዳይገጥማቸው የጤና ባለሙያ በመመደብ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል።

በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-05-02