ሀገሬ ቲቪ

ደሞዝ አልከፍል ያለው መንግሥት

የደቡብ ሱዳን ፀጥታ አስከባሪዎች፣ ሐኪሞችና ነርሶችን ጨምሮ ዉዝፍ ደሞዛቸዉ ያልተከፈላቸው ሰራተኞች ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መፍትሄ አልተሰጣቸውም። የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ደሞዝ ለመክፈል እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ለመሸፈን በነዳጅ ገቢ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የመንግሥት ወጪን ለመደገፍ የውስጥ የገቢ ምንጮች በቂ አይደሉም ይላል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ላይ ብዙ ተበድሯል. እ.ኤ.አ. በ2019 ባለሥልጣናት በሀገሪቱ ውስጥ መንገዶችን ለሚገነቡ የቻይና ኩባንያዎች በቀን 10 ሺሕ በርሜል ድፍድፍ ዘይት ለመመደብ ተስማምተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2018 ለ400 የሕግ አውጭዎች የግል መኪና ለመግዛት 40 ሺሕ ዶላር ብድር ለመስጠት የተላለፈው ውሳኔ አብዛኛው የመንግሥት ሰራተኞች አንጻራዊ በሆነ ድህነት ውስጥ በሚኖሩበት ሀገር ይህ መደረጉ በሰፊው ተችቷል፡፡

ብዙ ነርሶች እና አዋላጆች በወር ከ100 ዶላር በታች የሚያገኙ ሲሆን ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ ያነጋገራቸው አንዳንድ የመንግሥት ሰራተኞች በጁባ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ቤተሰቦቻቸውን ለመንከባከብ እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤት መልእክተኛ ቴሬዛ አኮል ‹‹ምግብ ውድ ነው እና ልጆቼን ለትምህርት ቤት ክፍያ ያስጨንቋቸዋል›› ብላለች፡፡ "የእኛ ሁኔታ መጥፎ ነው." አኮል ከጥር ወር ጀምሮ ክፍያ እንዳልተቀበለች ተናግራለች፡፡

ፕሬዚዳንት ኪር ባለፈው ዓመት የፋይናንሺያል ባለስልጣናት የደመወዝ ክፍያን መደበኛ ለማድረግ በቀን 5 ሺሕ በርሜል ድፍድፍ ዘይት እንዲመድቡ መመሪያ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም ያ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም፡፡
የደቡብ ሱዳን የገንዘብ ሚንስትር አጋክ አቹይል እንዳሉት ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ከዚሕ ቀደም ለተበደሯቸዉ አገልግሎቶች እየከፈሉ በመሆኑ ለሠራተኞች ደሞዝ የምንከፍው አጥተናል ብለዋል፡፡

"መንግስት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር እስከ 2027 ድረስ ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ የሚያገኘዉን ገቢ በሙሉ ለዕዳና በጣም አስፈላጊ ለተባሉ ጉዳዮች እያዋለው ነዉ። ይሁንና መስሪያ ቤታችን በቅርቡ ለመንግስት ሰራተኞች የጥቅምት፣የሕዳርና ታሕሳስ ወር ደሞዝ ከፍለናል፤ ቀሪዉ ለመክፈል ለ2028 እና ከዚያ በኋላ የሚመረተዉን ነዳጅ አስቀድሞ ለመሸጥ አቅድናል ብለዋል፡፡"

ደቡብ ሱዳን በዓመት 3.5 ቢሊዮን በርሜል ዘይት ታመርታለች፤ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ በወር የምታስገባዉ ገንዘብ 57 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡በተቃራኒው የመንግሥት የወር ወጪ ግን 200 ሚሊዮን ዶላር ነዉ፡፡
የአንዳንድ የመንግሥት ተቺዎች ብዙዎቹ ያለ ፓርላማ ዕውቅና የተጠናቀቁ በመሆናቸው መንግሥትን በሙስና የተጨማለቀ ብድር ወስዷል ሲሉ ይከሳሉ፡፡

"እነዚህ ብድሮች በጣም የተበላሹ ናቸው ምክንያቱም በጠረጴዛው ስር ብዙ ገንዘብ እየተለዋወጠ ነው" በማለት ቀደም ሲል ለመንግሥት ይሰሩ የነበሩት ኢኮኖሚስት ፒተር ቢ.አጃክ ተናግረዋል፡፡ "ለዚህም ነው የአምስት ዓመት ገንዘብ የጠፋው"

እ.ኤ.አ. በ2011 ሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ በመታገል ነፃነቷን ከሱዳን አግንታለች ፡፡ በደቡብ ሱዳን ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ተስፋ ተጥሎ የነበረ ሲሆን ይህ ተስፋዋ ብዙም አልዘለቀም፡፡
ሀገሪቱ በታህሳስ 2013 ወደ እርስ በርስ ጦርነት ገብታለች ፤እ.ኤ.አ. በ2018 በተጠናቀቀው የእርስ በእርስ ግጭት ኪር እና ማቻርን ወደ ብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲመለሱ ቢደረግም የእርስ በርስ ግጭት አስነስቶ በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ምርት እስካሁን ሙሉ በሙሉ አላገገመም፡፡ ሀገሪቷ ቀሪዉ እዳዋን ለመክፈል ለ2028 እና ከዚያ በኋላ የሚመረተዉን ነዳጅ አስቀድሞ መሸጥ መፍትሄ መሆኑን መንግሥት አምኖል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-11