የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወደፊት የሰው ልጆችን ሊቆጣጠር ይችላል ተባለ፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) መስራች እና አባት የሚባሉት ጀፍሪ ሒንተን ቻትጂፒቲን የመሰሉ ፈጠራዎች የሰው ልጅን መልሰው ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉት ፍንጭ ሰጡ።
ሳይንቲስቱ ይህን ፍንጭ የሰጡት ጎግል ኩባንያን ለቀው ሲወጡ ነው።
ሳይንቲስቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንዳንድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራዎች አስፈሪና አደገኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተንትነዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ) ፈጠራዎች ለጊዜው ከሰው ልጅ በላይ አልሆኑም፤ በጊዜ ሂደት ግን የሰው ልጅን ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የዶ/ር ሒንተን በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ልህቀት ዙሪያ ያደረጓቸው ጥናትና ምርምሮች ቻትጂፒቲን ለመሰሉ ትልልቅ ሥራዎች መፈጠር መሰረት የጣሉ ናቸው።
በወንድማገኝ አበበ
2023-05-02
