የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጋና ገብተዋል፡፡
የጃፓኑ ጥቅላይ ሚኒስቴር ፉሚዮ ኪሺዳ ወደ ጋና ማቅናታቸው ተነግሯል።
ፉሚዮ ኪሺዳ ከጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ ጋር በሀገራቱ ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደ ጋና ከማቅናታቸው በፊት በጃፓን_ግብፅ ቢዝነስ ፎረም ላይ በካይሮ ተሳትፈዋል።
ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋርም በአካባቢያዊ ጉዳዮች በፍልስጤም እና በሊቢያ ስላለው ሁኔታ እንዲሁም በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ወደ ኬንያ እና ሞዛምቢክ እንደሚጓዙም ተጠቁሟል።
በማህሌት አማረ
2023-05-02
