ሀገሬ ቲቪ

የስራ ሰዓት ማሻሻያ በጋምቤላ ክልል ተደረገ፡፡

የስራ ሰዓት ማሻሻያ በጋምቤላ ክልል ተደረገ፡፡

በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ የመንግሥት የስራ ሰዓት ወቅት ከነገ ጀምሮ ወደ ቀድሞው እንደሚመለስ የክልሉ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በለውጡ መሰረት ላለፉት ሶስት ወራት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ተኩል የነበረው ከ1 ስዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩል ሆኗል ተብሏል።

ከሰዓት በኋላም ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ተኩል የነበረው ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ተኩል ሆኖ ወደ ቀድሞው እንዲመለስ መደረጉ ተነግሯል።

የክልሉ የመንግሥት ሰራተኞችም ይህንኑ አውቀው በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደውን ስራቸውን እንዲያከናውኑ መነገሩን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በማህበራዊ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-05-08