8.2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ወደ ስራ እንደሚገቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።
ኮርፖሬሽኑ ከ10 ሀገር በቀል ኩባንያዎች ጋር የውል ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ግማሽ ያህሉ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ድርጅቶች መሆናቸው ተገልጿል።
በውል ስምምነቱ መሰረት አስሩ ኩባንያዎች በቦሌ ለሚ፣ በቂሊንጦ፣ በሰመራ፣ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በነፃ ንግድ ቀጠና በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ሲሆን በአጠቃላይ ከ7 ሺህ 400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በማህሌት አማረ
2023-05-08
