
ኢትዮጵያ ዘንድሮም ዓለም አቀፉን የአፍሪካ ኢኖቬሽን ዲጂታል ጉባዔ እንድታስተናግድ ተመርጣለች፡፡
ጉባዔው ሰኔ 7 እና 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ጉባዔውን በየዓመቱ እያካሄደች እንደምትገኝና ዘንድሮም በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ጉባዔው ኢትዮጵያ ለጀመረችው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያድርግ ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-05-09