ሀገሬ ቲቪ

በናፍጣ እና ቤንዚን የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን እና ይልቁንም ሶላር ኢነርጂ እና ሌሎች ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በናፍጣ እና ቤንዚን የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን እና ይልቁንም ሶላር ኢነርጂ እና ሌሎች ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የሚደርሱ 1 ሺህ 80 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል ተብሏል።

በዚህም 251 ሺህ ሄክታር ወደ ሥራ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

በዓመት 50 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልት የታሰበ ቢሆንም ክንውኑ በአምስት እጥፍ አድጓል።

በተጨማሪም ብልሽት አጋጥሟቸው የነበሩ 744 ፕሮጀክቶችም የተጠገኑ ሲሆን በዚህም 43 ሺህ ሄክታር ወደ ልማት መግባቱ ተነግሯል።

በበጋ ስንዴ 1.3 ሚሊዮን ሄክታር ለማልማት የታቀደ ሲሆን በቆላማ አካባቢዎችም ይህ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እና መሬት በማዘጋጀት ረገድም ጥሩ ተሞክሮ መኖሩ ተጠቁሟል፡፡

በወንድማገኝ አበበ
2023-05-09