ሀገሬ ቲቪ

ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ 60 ሺህ ቶን ወይም 600 ሺህ ኩንታል ግብይት መፈፀሙን ለሀገሬ ቲሌቪዥን ተናገረ፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ 60 ሺህ ቶን ወይም 600 ሺህ ኩንታል ግብይት መፈፀሙን ለሀገሬ ቲሌቪዥን ተናገረ፡፡

የምርት ገበያው ይህን ግብይት የፈፀመው የዘይት አቀነባባሪዎች እንዲገበያዩ ለማድረግ በከፈተው በልዩ መስኮት ነው፡፡ ይህ ግብይት የተፈፀመውም የምርት ገበያው ለዘይት አቀነባባሪ ፋብሪካዎች በዋናነት በሚያገበያየው ከአኩሪ አተር እና ከሰሊጥ መሆኑን ነግሮናል፡፡

እስካሁንም ከ40 በላይ የዘይት አቀነባባሪ ፋብሪካዎች በልዩ መስኮት ተመዝግበው ግብይት መፈፀማቸውንም ሰምተናል፡፡

በዚህ በልዩ መስኮት መሳተፍ የሚፈልጉ የዘይት አቀነባባሪ ፋብሪካዎች ማሟላት ያለባቸውን መረጃዎች በማሟላት ካኢንዲስትሪ ሚኒስቴር ፈቃድ በመውሰድ ገበያውን መቀላቀል እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-05-10