የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ።
8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 የሚሰጥ ሲሆን የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ቢሮ አስታውቋል።
ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።
በዘንድሮ የትምህርት ዘመን 75 ሺህ 100 የ8ኛ እንዲሁም 75 ሺህ 78 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-05-10
