ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን በጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ የሚከናወን አላግባብ እስር ተበራክቶ መቀጠሉን ገለፀ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን በጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ የሚከናወን አላግባብ እስር ተበራክቶ መቀጠሉን ገለፀ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሺነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው እስር ህግ ተላልፈዋል በሚል ቢሆንም ከስራቸው ጋር በተያያዘ መሆኑ የተስተዋለ ነው ብለዋል፡፡

በተደጋጋሚ ለእስር እየተጋለጡ ያሉ ጋዜጠኞችም ስለመኖራቸውም ጨምረው አንስተዋል።

ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ የቅድመ ምርመራ እስር ሊፈፀምባቸው የማይገባ ቢሆንም ድርጊቱ ተባባሶ መቀጠሉን የኮሚሽኑን የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ሲያቀርቡ ገልፀዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-05-10