ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ኒዝሃ አለዊ መሐመዲ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ያለውን ትብብር በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በግብርና ግብዓት እና የአፈር ማዳበሪያ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

የሁለቱን አገራት ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ይበልጥ በማስተሳሰር ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

አገራቱ በስታትስቲካል መረጃዎች አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም በእቅድና በልማት ስራዎች ክትትልና ድጋፍ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-05-10