የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱዳን የተከሰተውን ግጭት ማስቆም አለመቻሉን ገለፀ።
በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጄኔራሎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተጀመረውን ጦርነት ለማርገብ የተደረገው ጥረትም እንዳልተሳካ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ህዝቡን ወደ ከፋ ሁኔታ እየወሰደው መሆኑንም ገልፀዋል።
ጉቴሬዝ ሁለቱ ጄኔራሎች የገቡበትን ጦርነት አቁመው ወደ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲሸጋገሩ ሌሎች ሀገራት ግፊት ማድረግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
በናርዶስ ታምራት
2023-05-10
